『የዓለም ዜና』のカバーアート

የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

著者: DW
無料で聴く

このコンテンツについて

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።2025 DW 政治・政府
エピソード
  • DW Amharic የግንቦት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/06/07
    የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች “ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ” የሚል ጥሪ ያቀረቡበትን ትዕይንተ-ሕዝብ በበይነ-መረብ አካሔዱ። በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት ምክንያት የተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት እየተባባሰ” መሔዱን የአውሮፓ የሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ርዳታ ሥራ ክፍል አስታወቀ። በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ነዋሪዎች መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ። በዩክሬን ኻርካይቭ ላይ ሩሲያ በድሮኖች እና ሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የግንቦት 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/06/06
    አርዕሥተ ዜና -የኢድ አል አድሐ በዓል ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሙሊሞች ዘንድ መከበር ጀመረ።ከሱዳን እስከ ምያንማር፣ ከጋዛ እስከ ካሽሚር የሚደረጉ ጦርነት፣ ግጭትና የመብት ረገጣዎች የመንፈሳዊዉን በዓል ድባብ አጥልተዉበታል።የሐጂ ሥርዓት ግን እስከ ዛሬ ብዙ መጨናነቅና አደጋ አልታየበትም ተብሏል። -የሩሲያ ጦር በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈተ።የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ እንዳሉት አብዛኞቹ የየኩሬን ከተሞች «አረመኒያዊ» ባሉት ጥቃት ክፉኛ ተደብድበዋል።-ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች ላይ ማዕቀብ መጣልዋን ፍርድ ቤቱ አወገዘ። ድርጅቶች አጥብቀዉ ተቃወሙት።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ. ም. የዓለም ዜና
    2025/06/05
    *ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር "የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባችም" *የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2018 ዓ ም ሁለት ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት አጸደቀ *ትራምፕ የኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ አገዱ *ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የውጭ ዜጎች በዘንድሮ ሀጅ ተካፍለዋል *የዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ በፀጥታው ምክር ቤት ውጣ አጭሯል *የጀርመን መራኄ-መንግሥት ሜርዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኙ
    続きを読む 一部表示
    9 分

የዓለም ዜናに寄せられたリスナーの声

カスタマーレビュー:以下のタブを選択することで、他のサイトのレビューをご覧になれます。