エピソード

  • የሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
    8 分
  • DW Amharic የግንቦት 30 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/06/07
    የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች “ጦርነት ይቁም፣ ግፋዊ አገዛዝ ይብቃ፣ ሰላም ይምጣ” የሚል ጥሪ ያቀረቡበትን ትዕይንተ-ሕዝብ በበይነ-መረብ አካሔዱ። በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች “በፖለቲካዊ እና የብሔር ልዩነት ምክንያት የተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት እየተባባሰ” መሔዱን የአውሮፓ የሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ ርዳታ ሥራ ክፍል አስታወቀ። በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በጎርፍ 1,753 አባወራዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ነዋሪዎች መንደራቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጠ። በዩክሬን ኻርካይቭ ላይ ሩሲያ በድሮኖች እና ሚሳይሎች በፈጸመችው ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የግንቦት 29 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/06/06
    አርዕሥተ ዜና -የኢድ አል አድሐ በዓል ዛሬ በአብዛኛዉ ዓለም በሙሊሞች ዘንድ መከበር ጀመረ።ከሱዳን እስከ ምያንማር፣ ከጋዛ እስከ ካሽሚር የሚደረጉ ጦርነት፣ ግጭትና የመብት ረገጣዎች የመንፈሳዊዉን በዓል ድባብ አጥልተዉበታል።የሐጂ ሥርዓት ግን እስከ ዛሬ ብዙ መጨናነቅና አደጋ አልታየበትም ተብሏል። -የሩሲያ ጦር በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈተ።የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልድሚየር ዘለንስኪ እንዳሉት አብዛኞቹ የየኩሬን ከተሞች «አረመኒያዊ» ባሉት ጥቃት ክፉኛ ተደብድበዋል።-ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች ላይ ማዕቀብ መጣልዋን ፍርድ ቤቱ አወገዘ። ድርጅቶች አጥብቀዉ ተቃወሙት።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ. ም. የዓለም ዜና
    2025/06/05
    *ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር "የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባችም" *የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2018 ዓ ም ሁለት ትሪሊዮን የሚጠጋ በጀት አጸደቀ *ትራምፕ የኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች ዩናይትድ ስቴትስ እንዳይገቡ አገዱ *ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የውጭ ዜጎች በዘንድሮ ሀጅ ተካፍለዋል *የዩናይትድ ስቴትስ ውሳኔ በፀጥታው ምክር ቤት ውጣ አጭሯል *የጀርመን መራኄ-መንግሥት ሜርዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኙ
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • የግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    2025/06/04
    የግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና አንድ የዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ዛሬ በሱዳንዋ ምዕራብ ዳርፉር ግዛት ውስጥ በሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በቦምብ መመታቱን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ። ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እርዳታ የሚያከፋፈልባቸው ማዕከላት ለጊዜው መዘጋታቸውን በዩናይትድ ስቴትስና በእስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብዓዊ ድርጅት የተባለው ቡድን አስታወቀ። የአውሮፓ ኅብረት ዋነኛ የንግድ ተደራዳሪ ማሮስ ስፌሶቪክ ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ በብረታ ብረቶች ላይ በእጥፍ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጓ ድርድሩን የሚያግዝ እንደማይሆን ተናግረዋል።
    続きを読む 一部表示
    10 分
  • የግንቦት 26 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/06/03
    የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፖለቲከኞች ክልሉን ለዳግም ጦርነት ከሚዳርግ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ የሚደረገዉ ጥሪና ማሳሰቢያ እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት የገጠሙት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻና የሚያደርጉት ዝግጅት ዳግም ጦርነት ሊገጥሙ ነዉ የሚለዉን ሥጋት እያናረዉ ነዉ።---ለምዕራባዊ ሱዳን ግዛት ለዳፋር ሕዝብ የሚከፋፈል ርዳታ የጫኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሚዮኖች መደብደባቸዉን ድርጅቱ አስታወቀ።በጥቃቱ ሰዎች ተጎድተዋል።የሱዳን ጦርነት ያሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ደግሞ ከአራት ሚሊዮን በልጧል።-የሩሲያና የዩክሬን ጦር ኃይላት አንዳቸዉ የሌላቸዉን ይዞታ ማጥቃታቸዉን ዛሬም እንደመሰንበቻዉ ቀጥለዉ ዉለዋል።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የዓለም ዜና፤ ግንቦት 25 ቀን 2017 ሰኞ
    2025/06/02
    አርስተ ዜና አቶ ታዬ ደንደዓ ከዚህ በፊት ነጻ የተባሉባቸውን የክስ ጭብጦች በመሻር እንዲከላከሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ አዘዘ፡፡ በሌላ በኩል አቶ ታየ አሁን ከደቂቃዎች በፊት መታሰራቸዉ ተሰምቷል።--የቀድሞዋ የጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ በኒውዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጠቅላላ ጉባኤ መሪ ሆነዉ ተሾሙ።--ሳዑዲ አረቢያ የሐጂ መንፈሳዊ ጉዞ ወርን ጨምሮላልተወሰነ ጊዜ ኢትዮጵያ ጨምሮ ለሰባት አፍሪቃ ሃገራት ዜጎች የሥራ ቪዛ መስጠት ማቋረጥዋን አስታወቀች።--ሚልዮን የሚቆጠሩ ሙስሊም ምዕመናን ከዓመታዊው የሐጅ መንፈሳዊ ጉዞ በፊት ወደ ቅድስት ከተማ መካ እየገቡ ነዉ።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • የግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ ም የዓለም ዜና
    2025/06/01
    *ናይጄሪያ ውስጥ 22 አትሉቶች በአውቶቢስ አደጋ ሞቱ *ህገ ወጥ አፍሪካውያን ስደተኞች ከቲኒዚያ መመለስ ይሻሉ *ዩክሬን ከ 40 በላይ የሩሲያ አይሮፕኖችን አወደምኩ አለች *ኢራን ከአውሮፓ ማዕቀብ ቢጣልባት አጸፋ እንደምትወስድ ዛተች *ከቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በኋላ በፈረንሳይ ሁለት ሰዎች ተገደሉ፣ በመቶዎች ታሰሩ
    続きを読む 一部表示
    8 分